The AAC market cards were created in response to a desire from the families that their children be able to participate in a typical activity for Ghanaian children: buying food for the family at the market. The AAC market cards have the name and picture of the item the students are to buy for their families. The cards also have the cost; that is how much of the item the family wants the student to buy. How to use the cards has been disseminated through annual professional development retreats so they are now used by students with autism, intellectual disabilities, and cerebral palsy throughout Ghana.
The transcript for this video in Amharic is below:
 ሰላም ስሜ ኬት ክራወሊ እባላለሁ በመምህራን ኮሌጅ የኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ መምህር ነኝ።
ዛሬ አንድ ከእናንተ ጋር ላጋራችሁ የምፈልገው ኤኤሲ የገበያ ካርድ ስለሚባልነው። ይህ ካርድ መናገር ለተሳናቸው ተማሪዎች ጥሩ የግብይይት ዘዴ ነው።
ስራችንን የጀመርነው በጋና በኦፊዱሲ ወረዳ የአይምሮ ጉዳተኞች ት/ቤት መምህር ሃላፊ ከሆኑት ከወ/ሪት ቤለንዳ ቡከራ ጋር ነው። ወደ ጋና ስንሄድ ወላጆችን ” ልጆቻችሁ ማድረግ ያልቻሉት ግን እንዲያደርጉላችሁ የምትፈልጉት ነገር ምንድን ነው?” ብለን ጠየቅናቸው
ወላጆቹም እንደማንኛውም ጤነኛ ልጅ ገበያ እንዲላኩልን ነው አሉን ፣ መምህራንም ልጆች ለወላጆቻቸው ገበያ መላላክ የጋናውያን ባህል መሆኑን ከአረጋገጡልን በኋላ፣ ወዲያውኑ ኤኤሲ የመግባቢያ ዘዴ ካርድ ለማዛጀት ወሰንን። ካርዱ ገበያ ሲገበያዩ “ምን መግዛት እንደሚልጉ እና በምን ያህል ዋጋ እንደሚገዙ በቀላሉ በሚገልጽ ካርድ ነው።
መጀመሪያ በገበያ ውስጥ የአብዛኛውን ዕቃ የመሸጫ ዋጋ በ 20 ብር በ10 ብር 1 ብር መሆኑን ካረጋገጥን በኋላ፣ ይህንን አይነት የገበያ ካርድ አዘጋጀን።
1. ይህ የምታዩት በ20 ብር ፓፓዬ ካርድ ነው ሌላ ሁለት በ10ብር ፓፓዬ 1ብር ፓፓዩ ካርድ አሉን።
2. ከዚያም በብላስቲክ ጠርዘነው ካርዱን እንደምታዩት ብዙም የሚያምር ባይሆንም ስራው ግን ውጤታማ ነበር። በእርግጥ ከሁሉም በፊት ከተማሪዎች ጋር በክፍል ውስጥ በሚገባ ልምምድ አድርገናል። ከዛም ለወላጆች ልጆቻቸው ከገበያ እንዲገዙላቸው የሚፈልጉትን ነገር ባለ20 ብር ፓፓዬ፣ ባለ50ብር ሩዝ፣ በካርዱ መሰረት እንዲሰጧቸው ልጆችን ካርዱን ይዘው ወደ ገበያ እንዲሄዱ አደረግን፣
3. አሁን ከተማሪዎች ጋር ወደ አካባቢ ገበያ ሄደን እናት ነጋዴዎች ተማሪዎችን በስም ስለሚያውቋቸው ተማሪዎች በተረጋጋ መንፈስ ነበር የሚገበያዩት በመጀመሪያ እናት ነጋዴዎች የመናገር ችግር ያለባቸው ልጆች ምግባቸው ለመገበያየት የሚያደርጉትን ሙከራ ልብ የሚነካ ቢሆንም አንዲት እናት ነጋዴ እንዲህ ሲሉ ተደምጠዋል። ” ወይ ጉድ እነዚህ አሜሪካውያኖች ከልጆቻችን ጋር ከተግባቡ እኛም ማድረግ እንችላለን ማለት ነው” ብለዋል።
ለእኔ የመናገር ችግር ያለባቸው ተማሪዎች በአካባቢያቸው መፍትሄ የሚሆን የግንኙነት ዘዴ መፍጠር እና ተግባራዊ ማድረግ ውጤታማ እንደሚሆን ይህ ጥሩ ምሳሌ ነው።
አመሰግናለሁ።
Find the playlist for the full set of videos in this module series here: